ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
89

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአምባጊዮርጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለከተማ አስተዳደሩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያ እስቴሽነሪ ፣ሎት 2 የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 4 የመኪና እቃ መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡ የመወዳደሪያ መስፈርቶቹም፦

  1. በየዘርፍ የዘመኑን የታደስ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለማሸነፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና ናሙና የሚያስፈልጋቸው ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 ዘወትር በሥራ ስዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የተስተካከለ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
  8. የጨረታ አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በተናጠል በየሎት ምድባቸው የሚለይ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፋያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. በጨረታ 1ኛ የወጣውን ውል እስከሚወስዱ ድረስ 2ኛ የወጣው የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስለትም፡፡
  11. አሸናፊው አሸናፊነቱን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአምባጎርጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሥዓት ማስታወቂያው ጋዜጣ ከወጣበት 26/05/2017 ዓ.ም እስከ 10/06/2017 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ጨረታውን መግዛት ይችላሉ፡፡
  13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 11/06/2017 ዓም በተዘጋጀው ሳጥን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ብሔራዊ በዓል ከሆነ የሚቀጥለው ቀን
    ይሆናል፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከአምባጎርጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 118 08 46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአምባጊዮርጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here