ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
93

የላይ አ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በትክል ድንጋይ ከተማ ውስጥ በመንግስት እዳ ተይዞ በፍርድ ቤት ውሳኔ ተሸጦ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን የላይ አርማጭሆ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በፃፈው ደብዳቤ መሰረት በካርታ ቁጥር ቀስ/ግ/-39/2008 የተመዘገበ ስፋቱ 114.13 ካ/ሜ በታ ላይ ያረፈ ቤት የመነሻ ዋጋ ብር 418,653.02/ አራት መቶ አስራ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ሶስት ብር ከ02 ሳንቲም/ ሲሆን በገልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስስዚህ መግዛት የምትፈልጉ ግለሰቦች በሙሉ መጫረት የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡

  1. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት እስከ 21 ኛው ቀን ድረስ ሰነዱን በመግዛት በላይ አ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በመገዛት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  2. ጨረታው በወጣ በ22 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዚያኑ ቀን በ4፡00 በግልጽ ይከፈታል፡፡
  3. ዝርዝር መረጃዉን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከሚገኝ ማስታወቂያ ታገኛላችሁ፡፡

ማሳሰቢያ፦ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የላይ አ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here