በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የተስፋዬ ጌታቸው መታሰቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ እና በውስጥ በጀት ለተስፋዬ ጌታቸው መታሰቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-ተጫራቾች ማሟላት የሚፈለግባቸው መስፈርቶች
- ህጋዊ /ወቅታዊ/ የታደሰ በዘርፍ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና /ቲን ካርድ/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችሉ እና አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውንና ሌሎች መረጃዎችን በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡20 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
- የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ /ማሻሻያ/ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፍ የሚደርጉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፍታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 26 መውሰድ ይቻላል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 058 667 06 35 ዘወትር በሥራ ሰዓት ደዉለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የተስፋየ ጌታቸው መ/የመ/ደረጃ ሆስፒታል