ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
109

ድርጅታችን መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒዬን ኃ.የተ. ከተለያዩ ስኳር ፋብሪካ 1101 ኩ/ል ስኳር ሎት 1 እና 10600 ኩ/ል ሰብል ሎት 2 ከተለያዩ የወረዳ ቀበሌዎች ወደ ዩኒዬኑ ሰብል ማራገፊያ ማዕከላዊ መጋዘን ደ/ታቦር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት መሳተፍ የሚፈልጉ እና በደረቅ ጭነት አጓጓዥነት የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች /ግለሰቦች አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ዝርዝር ሁኔታውን በጨረታ ሰነዱ የተካተተ ሲሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየጋበዝን፡-

  1. በዚህ ንግድ ዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤ከመንግስት የሚጠበቀረባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በሚቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ስማቸውን ፣ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ /ዋስት/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን የትራንስፖርት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ መገናኛ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን እና ተጫራቾች መመሪያውን በማይመለስ 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በመክፈል በመግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-4 የተዘረዘሩትን ሰነድ በመግዛት ዋጋቸውን ሞልተው በፖስታ በማሸግ በዩኒዬኑ ቢሮ በደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ፣ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ይህ ማስታዎቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ተሸጦ በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት በ8፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 10ኛው የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. ለስኳር ተጫራቾች ቢያንስ 200.00 (ሁለት መቶ) ኩ/ል እና ከዚያ በላይ መጫን የሚችል መኪና/ መኪኖች ያላቸው እና የመኪናውን የሊብሬ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ሲጠየቁ ዋናውን ሊቢሬ ማቅረብ /የመኪናውን ሊብሬ በብድር ከተያዘ ከባንኩ ህጋዊ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ስኳሩ ከሚነሳበት ቦታ (ፋብሪካ) ላይ 7 (ሰባት) ቀን እና ሰብል እንዲነሳ በተጠየቀ 03 ለሶስት/ ቀን ውስጥ ማንሳት የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
  9. ዋጋዉ ፀንቶ የሚቆየዉ አሸናፊዉ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ለ6 (ስድስት) ተከታታይ ወራት የሚቆይ፡፡
  10. አሸናፊዉ የሚለየዉ በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ የሞላዉ የሚሆን ሲሆን አሸናፊዉ በተለየ በ5 ቀን ዉስጥ የውል ማስከበሪያ የዋጋውን አስር በመቶ ሲፒኦ በማስያዝ ውል መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡
  11. ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀ/ሥ/ማ/ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
  13. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /058 141 28 64 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

መገናኛ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒዬን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here