ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
89

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ለ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ ንብረት ለሆኑት የተለያዩ ከባድ ተሸከርካሪዎች ጎማ ከነ ካላማዳሪዉና ከነፍላፑ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. በስሙ የታተመ ማህተምና ደረሰኝ ያላቸዉ፡፡
  4. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጫራቾች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ መስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 200,000,00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት 03/06/2017 ዓ.ም እስከ 18/06/2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሽህ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በዚሁ ቀን በ18/06/2017 ዓ.ም ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታዉን ለመክፈት እንገደዳለን፡፡
  11. አሽናፊዉ የሚለየዉ በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ባቀረበ ይሆናል፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች በባ/ዳር ከ/አስ/መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማጓጓዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በባ/ዳር ከ/አስ/መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብረት አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 18 78 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here