ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
86

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የወገዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ትብ//ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ፣ አላቂ የቢሮ እቃ፣ ቋሚ እቃ፣ የጽዳት እቃ፣ ህትመት የመብራት አክሰሰሪ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊዉን ማስቀረብ  ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ /ወቅታዊ/ የዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ማስረጃዉን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በሰነዱ ላይ የሞላው አጠቃላይ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸዉን ለእያዳዳቸዉ 00 /አንድ መቶ ብር/ የማይመለስ ገንዘብ በመክፈል የግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን መዉሰድ ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን እና ሌሎች መረጃዎችን በፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት በወገዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ት ጽ/ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው በ16ተኛው ቀን በዚሁ እለት በ3፡30 ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተቀመጠው ስዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባይኖሩም ለመክፈት አያስተጓጉሉም፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የእቃዉን ጠቅላላ ዋጋ ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ ደረሰኝ በመሂ 1 በመቁረጥ ኮፒ አድርገዉ በጨረታ ፖስታዉ ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊነታቸዉ እንደተገለፀላቸዉ  የዉል ማስከበሪያ አስር በመቶ በመ/ቤቱ  ደረሰኝ ወይም በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ማንኛውንም ወጭ ያጠቃለለ መሆን ይኖርበታል፡፡
  8. ተጫራቾች ከመወዳደሪያ ሃሳቡ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውንና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  9. የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ማሻሻያ ማድረግ እና በጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡ ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ እና ለወደፊቱም ከመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፍ የሚደረጉ መሆኑን እንገልጻን፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ጨረታዉ በመሰረዙ ተጫራቾች ላወጡት ዋጋ ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  11. መ/ቤቱ ከጨረታ አሸናፊው የሚፈለገውን አገልግሎት ጥራቱን ሳይቀይር በመመሪያዉ መሰረት ሊጨምር /ሊቀንስ/ ይችላል፡፡ ለበለጠ ማብራሪያ ወገዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ት ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 058 667 04 03 እና 058 667 03 89 እንዲሁም በአካል በመቅረብ  መረዳት ይቻላል፡፡

የወገዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ትብ//ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here