ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
85

በምዕራብ ጎጃም ዞን  የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ የሚገኘውን  ቁርጥራጭ ብረታ ብረት  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው የምትሳተፉ ድርጅቶች /ግለሰቦች/ በቀረበው የጨረታ ዝርዝር በንግድ ፈቃዱ መሰረት  መወዳደር ይችላሉ፡፡ ስለሆነም፡-የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፣ ተወዳዳሪዎች

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው ከ200,000.00 ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ግዥውን ግምታዊ ዋጋ መሰረት በማድረግ 50,000.00 (አምሳ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ /ሲፒኦ/ በኮሌጁ ስም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ መቆያ ጊዜ ከ 03/06/2017 ዓ.ም እስከ 17/06/2017 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ የጨረታ መወዳደሪያውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 18/06/2017 ዓ.ም እስከ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን ማለትም 18/06/2017 ዓ.ም ሲሆን ከረፋዱ 4፡00 የጨረታ ሳጥን ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በ 18/06/2017 ዓ.ም በእለቱ በ4፡30  ጨረታው የሚከፈት ሁኖ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 058 774 07 71 ደውሎ ወይም በአካል ቀርቦ /ማየት/ መረዳት ይቻላል፡፡
  10. አሸናፊው ድርጅት ውል ከያዘ በኋላ የሚጠበቅበትን ክፍያ በመክፈል ንብረቱን መረከብ ይኖበታል፡፡
  11. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  12. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት /ግለሰብ/ ማሸነፉን በተገለፀ ከአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት  ውስጥ  ውል ካልያዘ የጨረታ ማስከበሪያው ውርስ ይሆናል፡፡
  13. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለፁ ነገሮች ካሉ በግዥ መመሪያው  መሰረት ተግባራዊ  ይሆናሉ፡፡
  14. አሸናፊ ድርጅቱ /ግለሰቡ/ የሚዛን እና ሌሎች ወጭዎች በራሱ ሂሳብ ይሆናል፡፡
  15. የጨረታ ሰነዱን ከኮሌጁ ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 የማይመለስ በ400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ   ይቻላል፡፡

የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here