በወልዲያ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የመንግስት የልማት ድርጅት የሆነው ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በ2017 በጀት አመት ለሚገነባው የከሚሴ እናቶች እና ህጻናት ሆስፒታል ህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት የሚውል ሎት 1 ሴራሚክና ፎርስሊን ንጣፍ አቅርቦት እና ሎት 2 ለመንገድ ማስዋብ ግንባታ የሚውል ባዞላ/ colour chequered Terarazo) አቅርቦት በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊና ብቃት ካላቸው ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራች በሥራ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፊኬት ያላቸውና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ፣ ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በተረጋገጠ ሲፒኦ የባንክ ጋራንቲ ዋና /ኦርጅናል/ ዶክመንት ሰነዶች ጋር አያይዘው አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክና ኢንሹራንስ ማቅረብ አይቻልም የተከለከለ ነው ተቀባይነትም የለውም፡፡
- ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ በእያንዳንዱ ሎት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ወልዲያ ከተማ ጎማጣ በሚገኘው ከኢንተርፕራይዙ ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ15ኛው ቀን 11:00 ላይ ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ላይ በኢንተርፕራይዙ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አያግደውም፡፡
- ክፍያን በተመለከተ በሁሉም ሎቶች በአማካሪዎች የጸደቀ በማቅረብና በጸደቀ ሳምፕል መሰረት ቦታው ድረስ ማቅረብ ሲችሉ ነው፡፡
- በጨረታው ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታ ውጤቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ብቻ ቅሬታው ማቅረብ ይችላል፡፡
- ማንኛወም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክሰን ጨምሮ መሙላት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የተከለከለ ነው፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 13 50 49 72 /09 12 91 82 14 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ