በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ ሎት 1. የአምሰት ዓመት እስትራቴጅክ ፕላን ለማስጠናት እና ሎት 2. የስከኳር ማጓጓዝ ደረጃ አራት አጓጓዥ ድርጅት እና ከዚያ በላይ ማቅረብ እና ለአንድ አመት በየዙሩ ከሚመደብልን ቦታ ውል በመያዝ ለማጓጓዝ ፈቃደኛ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መጫረት ይችላሉ፡፡
- በዘርፍ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- የዩንየኑን ዋና ዋና ተግባራት እና የሥራ ዘርፎች ለቀጣይ አምስት አመት እቅድ መስራት የሚችል እና የጥናቱን መነሻ መረጃ ከሥራ ክልሉ እና ከዩንየኑ ሙሉ መረጃ በእየ ዘርፍ በመውሰድ መስራት የሚችል፡፡
- ለቀጣይ ዓመት እቅዱ በየአመቱ እየተሻሻለ የሚተገበር የሚችል እና የቀጣይ የገቢያውን የአካባቢውን ሁኔታ የሀገሪቱን ነባራዊ ሆኔታ እና ማህበራዊ እና ኢኮኖሜያዊ ሁኔታ ተንትኖ በጥናት ላይ የተመሰረት ጥናት በማድርግ መሰራት የሚችል እና ሶስት እና ከዚያ በላይ የሰሩበት የተቋማት የሥራ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ሚሰበሰበው መረጃ የዳሞትን የሥራ ክልል መሠረት ተደርጎ በተጨባጭ መረጃ ላይ ተመስርቶ መረጃ ማስባሰብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ፓስታ ውስጥ በማስገባት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩንየኒ ሂሳብ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በራስዎ ማህተም በተዘጋጀ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለተከታታይ 11 የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ ተለጥፎ ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች በተገኙበት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አይስተጓጎልም፡፡
- ጨረታውን ያሽነፈ ተጫራች ጨረታው ተከፈቶ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር አስር በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ የተያዘው ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡ አሸናፊው የስኳር ማጓጓዝ ተጫራች የጭነት ማዘጃና ዲስፓች ማዘጋጀት አለበት፡፡
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱት ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 774 06 40 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መጠየቅ እና መስተናገድ ይችላሉ፡፡
የዳሞት የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ