ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
104

የሞጣ ፖ/ቴ/ኮሌጅ 2017 ዓ.ም ለትምህርት ሥልጠናና ለቢሮ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጥሬ እቃዎች 1 የህንፃ መሳሪያ እቃዎች፣ 2 የኤሌክትሪክ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ 3. የኮምፒውተር እቃዎች፣ 4. የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ 5 የጨርቃ ጨርቅ እቃዎች፣ 6.ግብርና እቃዎች እና 7. የኢንዱስትሪ እቃዎች በጋዜጣ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. ማንኛውም ህጋዊና የታደሰ የንግድ /የሥራ ፈቃድ/ ያላቸውና ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ ቁጥር /ቲን/ የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በማንኛውም ጨረታ እንዳይሳተፍ እግድ ያልተጣለባቸው መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች /የቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑና የቫት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  4. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ የጨረታ ቦታ ሞጣ /ፖ/ኮሌ/ግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀናት ከረፋዱ 4፡00 ድረስ በታሸገ ፖስታ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በመክፈቻ ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ኮሌጁ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  5. ተጫራቾች የንግድ ፈቃዳቸውን፣ ቲን ናምበራቸውን፣ ቫት ሪጅስተራቸውን ከዋጋ ማቅረቢያ ፖስታቸው ጋር ኮፒ አድርገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000 /ሁለት ሺህ ብር/ ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያውን ዋስትና ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ በግልጽ ጽሁፍ በመጻፍና በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን ስማቸውን እና ፊርማቸውን ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ጨረታ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ የውሉን ዋጋ አስር በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለበት፣ ቀርበው ተገቢውን ውል ባይፈጽሙ የጨረታ ማስከበሪያውን ውርስ አድርጎ ኮሌጁ የራሱን አማራጭ ይወስዳል፡፡
  10. የክፍያ ሁኔታ ውል የያዘባቸው /ግዴታ የገባበትን/ ዕቃ ሙሉ በሙሉ በባለሙያ ተረጋግጦ ለኮሌጁ ንብረት ክፍል በራሱ ወጭ እቃዎችን አቅርቦ ገቢ ሲያርግና ሞዴል 19 ሲያቀርብ ሙሉ በሙሉ ክፍያ ይፈፀምለታል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከኮሌጁ ገንዘብ ያዥ ብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥር 058 661 04 32 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  12. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሆኖ ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ ኮሌጁ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የሞጣ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here