ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
104

በማእከላዊ ጎንደር ዞን የአይከል ሆስፒታል ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ አቅርቦቶችም፡- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የህትመት ግዥ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4 የዉሃ እቃዎች፣ ሎት 5 የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 7 የኦክስጅን ሙሊት ግዥ እና ሎት 8 የኦክስጅን ጭነት የትራንስፖርት ዋጋ ግዥ ናቸዉ፡፡ እስከተቻለ ድረስ ውድድሩ በሎት ጠቅላላ ድምር ወይም በነጠላ ድምር ይሆናል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  4. የሎት የግዥው መጠን ብር000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውን በጀርባው ላይ ከዋናው ጋር ተገናዝቧል ብሎ በመፃፍ ማህተም፣ ስም ፊርማና ቀን በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃዎችን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
  7. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላሉ፡፡ በተጨማሪም ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸዉ እቃዎች ሆስፒታሉ ድረስ በመምጣት ማየት የሚችሉ መሆኑን ጨምረን እንገልጻለን፡፡
  8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ማስረጃ ቢያስፈልጋቸው ከቡድን መሪዉ ቢሮ ቁጥር 51 ወይም በስልክ ቁጥር 058 333 01 83 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከላይ ከተጠቀሰው አድራሻ መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዱን ዋስት ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት አንድ በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  11. ጨረታዉን ያሸነፈዉ ተጫራች የዉል ማስከበሪያ ጠቅላላ የሎት ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ በጭልጋ ወረዳ ፍ/ጽ/ቤት ዉል መያዝ ሚችል መሆን አለባቸው፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቱበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ ስማቸውንና አድራሻቸውን በመፃፍ በአይከል ሆስፒታል ውስጥ ከግዥ ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቅያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመርያ ቀን ጀምሮ የሚውል ሲሆን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
  13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአይከል ሆስፒታል አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  14. ጨረታው ሲሞላ ሥርዝ ድልዝ ካለው ጨረታው ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይሆናል፡፡ ሥረዝ ድልዝ ካጋጠመ ፓራፍ /ፊርማ/ ማድረግ ይገባል፡፡ ካልተደረገ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
  15. የጨረታ አሸናፊውን የምንለየው በሎት ድምር ወይም በነጠላ ድምር ይሆናል፡፡
  16. መ/ቤቱ ከጨረታዉ ከእያንዳንዱ ሎት ሃያ በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች በሳምፕሉ መሰረት ባይቀርቡ በኪሳራው መ/ቤቱ የማይጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  19. አሽናፊዉ ተጫራቾች በተቀመጠላቸው ስፔስፊኬሽን መስረት እና ሆስፒታሉ በመረጠው የጥራት ኮሚቴ ተረጋግጦ በተጠየቀው መሰረት ካልቀረበ በኪሳራው ሆስፒታሉ የማይጠየቅ መሆኑን ጨምረን እንገልፃለን፡፡
  20. የጨረታዉ መክፈቻ ቀን ካላንደር ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  21. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ የድርጅታቸዉን ክብ ማህተም ማድረግ አለባቸዉ

ማሳሰቢያ፡- አሸናፊው ድርጅት በአሽነፈው መሰረት እቃዎችን ሆስፒታሉ ድረስ ማቅረብ የሚችልና ውሉን በጭልጋ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ቀርቦ መውሰድ የሚችል መሆን አለበት፡፡

የአይከል ሆስፒታል

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here