በድጋሚ የወጣ የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
107

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ፍርድ ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 2 አነስተኛ የቢሮ እቃዎች እና ሎት 3 የህንፃ መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-2 የተጠቀሱት የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ማለትም ቲን ናምበር፣ ንግድ ፈቃድ ቫት ለሚያስፈልጋቸው ግዥዎች የቫት ሰርተፊኬት እና በውክልና የሚሰሩ ከሆነ የውክልና ወረቀት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ከፖስታው ውጭ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ካስፈለገ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በመሥሪያ ቤቱ አካውንት በማስገባት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን ከደጥ/ግን ወረዳ ፍርድ ቤት በ50 /ሃምሳ ብር/ ይሸጣል፡፡ ከኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በስተቀር የእቃው ዋጋ ከ200,000 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የድርጅታቸውን አድራሻ በመግለጽ እና በታሸገ ፖስታ እና ማህትም በማሳረፍ ደ/ጥ/ግን ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. መ/ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ በሎት የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. መ/ቤቱ ከጨረታው ከአሸናፊ ላይ ሁለት በመቶ ታክስ የሚቆረጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  10. ማንኛውም አሸናፊ እቃውን ገቢ በሚያደርግበት ወቅት ጥራቱን በባለሙያ ተረጋግጦና የታሸጉ እቃዎችን ተፈተውና ታይተው የምንረከብ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  11. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸ በኋላ የውል ማስከበሪያ አጠቃላይ ከተወዳደሩበት አስር በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12. ጨረታው በጋዜጣ /ድህረ ገጽ/ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 ሲሆን በዚሁ ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ በ16ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታ በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ የጨረታውን መክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ደ/ጥ/ግን/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 2570281 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. የጨረታው መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ካቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ እንዲታውቁ፡፡
  15. ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው እስከ ሃያ በመቶ ለመጨመር ወይም ለመቀነስ እንደሚችል ይታወቅ፡፡
  16. የጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ሥርዝ ድልዝ ካለበት መፈረም አለበት፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ደ/ጥ/ግን/ወ/ፍ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 257 01 19 /058 257 02 81 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here