የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ለ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. ህትመት፣ ሎት 3. የመኪና ጐማ፣ ሎት4. የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት5. ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 6. የጽዳት አገልግሎት /አመታዊ ኩንትራት/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት መሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዕቃዎችን ዓይነቶችንና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከአብክመ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ቢሮ ቁጥር 002 ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንድ የማይመለስ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የኮሚሽኑ ካርኒ በተቆረጠበት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከግዥ ባለሙያዎች ቢሮ ቁጥር 007 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት ተለጥፎ የሚውል ሲሆን የመጫረቻ ሰነዱንም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ባለሙያዎች ክፍል 007 በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጐ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አይስተጓጐልም፣ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ኮሚሽኑ ሃያ በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው የሚለየው ሁሉም ሎቶዎች በድምር ዋጋ ሲሆን ሎት 3 እና ሎት 5 በነጠላ ዋጋ ይሆናል፡፡
- ሰለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 03 79 መደወልና ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን
ባህር ዳር