በደ/ጎንደር ዞን የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግን/አስ ቡድን ለ2017 በጀት አመት ሎት 1 ት/ት/ጽ/ቤት ለአዲስ አለም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከደረጃ 7 በላይ ያላቸውን ተጀምሮ የቀረውን ግንባታ በክልል እና በወረዳ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰገንባት ይፈልጋል፡፡ በመደበኛ በጀት ሎት 2 የጽህፈት መሳርያ፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4 የጽዳት እቃ እና ሎት 5 የመኪና ጎማ ግዥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟሉ መጫረት የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡-
- በየዘርፉ ህጋዊ ፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቲን ካርድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከ200‚000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻቸውን በድርጅቱ ስም የተዘጋጀ ማህተም መምታት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በሥራ ቀን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ /በመሂ1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ (በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ለ15 ተከታታይ ቀን ተለጥፎ ይቆያል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ3፡00 ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ጨረታውን ለመክፈት ቢገኙም ባይገኙም ለመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- በማስታወቂያ ያልተገለጹ ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- የመልካም ሥራ አፈጻጸም መገለጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይደረጋሉ። ለወደፊቱም በመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፉ የሚደረጉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- የጨረታ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደርያ ሃሳብ ላይ ለወጥ (ማሻሻያ) ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስ/ቁ 09 18 28 07 69 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት