የጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብ /አ/ቡድን መሪ በበጀት ዓመቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 የእህል አቅርቦት፣ ሎት 2 የወጥ ማጣፈጫ፣ ሎት 3 አትክልትና ፍራፍሬ፣ ሎት 4 የማገዶ እንጨት፣ ሎት 5 ዘይትና ፊኖ፣ ሎት 6 እስቴሽነሪ፣ ሎት 7 የግንባታ ዕቃዎች፣ ሎት 8 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 9 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ከሎት 1 እስከ ሎት 5 ያሉትን ለ6 ወር ውል ወስዶ ከተቋሙ ድረስ የሚያቀርቡ ሲሆን ከሎት 6 እስከ ሎት 9 ደግሞ በወቅቱ ገዝቶ መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ የሚችሉትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን ከዚህ በታች ያሉ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ የሚያቀርቡ፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ለግዥ ፋይ/ንብ/አስ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ የሚሞሉትን አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፕኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የአሸነፈውን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈውን እቃ ጭልጋ ማረሚያ ቤት መጋዝን ድረስ የሚያቀርብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ቅጅዎች ማለትም ዋናውንና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ ቡድን መሪ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በተከታታይ ቀናት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከየካቲት 10 ቀን 2017 እስከ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ/ም እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርበቸዋል፡፡ የጨረታው ሳጥን የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ ቡድን መሪ ቢሮ የካቲት 25 ቀን 2017 ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃና ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 333 00 09 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ:-
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
- በሎት የተዘረዘሩት እቃዎች በጥቅል ዋጋቸው አሸናፊው ይለያል፡፡
- በሎት የተዘረዘሩት ናሙና ማቅረብ ያስፈልጋል ፡፡
የጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት