በአፈ/ከሳሽ እነ ዘመናይ አድማስ 2ቱ እና በአፈ/ተከሳሽ እነ 1ኛ አብርሃም መስፍን ፣2ኛ ያየሰው መርከቡ መካካል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 05 በአዋሳኝ በምሥራቅ 017፣ በምዕራብ 015፣ በሰሜን 018 እንዲሁም በደቡብ መንገድ የሚያዋስነው በ2ኛ አፈ/ተከሳሽ አቶ ያየሰው መርከቡ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት የሆነው መነሻ ዋጋ 2,990,540 /ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሺህ አምስት መቶ አርባ ብር/ ስሰሚሸጥ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 09 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ተለጥፎ መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከ3፡00 እስከ 6:00 የሚቆይ መሆኑን አውቃችሁ ቦታው ድረስ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 /በሲፒኦ/ አሲይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍ/ቤት