ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
92

በእንጅባራ ከተማ የሚገኘው የአዊ ልማት ማህበር ፈርኒቸር፣ ፍራሽ፣ ቲቪ፣ ፁሑፍ እና መጋረጃ  አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ግዥው ከ200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት  ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት  የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት ጠቅላላ ዋጋውን (ታክሱን ጨምሮ) በመሙላት  በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ጨረታ ማስከበሪያውን  ለየብቻ በመለያየትና በአንድ ፖስታ በማሸግ  ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ላይ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን በጋዜጣ ከወጣ በ16ተኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  7. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊ ድርጅት አስር በመቶ ውል ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  9. የተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስላቸው አሸናፊው ውል ከያዘ በኋላ ነው፡፡
  10. ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 227 03 62 /058 227 11 88 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አዊ ልማት ማህበር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here