ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
101

የአብክመ ገቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ግዥ በግልጽ ጨረታ አዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ እና ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ለሚጠይቁ ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ብር የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የሚሞሉቱን ጠቅላላ ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና የሚወዳደሩ ከሆነ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአብክመ ገቢዎች ቢሮ ባህርዳር ቢሮ ቁጥር 313 የቢሮ ህንፃ ለሁሉም ከላይ የተገለፀዉን ግዥ የማይመለስ ብር 200 ( ሁለት መቶ ብር ) ሰነዱን በመግዛት የነጠላ ዋጋ እና ጥቅል ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 313 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቅዳሜ እስከ 6፡30 ጀምሮ ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 313 ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
  7. (16ኛዉ) ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ ማንኛውንም ወጭ ራሱ ችሎ ለቢሮው አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች ያስረክባል፡፡
  9. ቢሮዉ በማንኛውም ሰዓት ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

አድራሻችን፡- ባህር ዳር ቀበሌ 16 ሜድሮክ ግብርና ምርምር ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 058 226 57 65 ወይም 058 226 61 71 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአብክመ ገቢዎች ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here