ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
102

የባህር ዳር ደም ባንክ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎች ከዚህ በታች በተከፋፈሉት ሎቶች መሰረት ማለትም፡- ሎት 1. የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2. የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3. የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 4. የደህንነት ካሜራ፣ ሎት 5. የመኪና ጎማ፣ ሎት 6. የደንብ ልብስ እና ሎት 7. የሴትና የወንድ ጫማ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ  በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ካርድ ወይም ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  4. አጠቃላይ የግዥው መጠን ከ200,000 (ሁለት ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ እቃዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለዕቃው ዓይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩ የዕቃ ዓይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችልም፡፡ ውድድሩ በሎት ጠቅላላ ድምር ውጤት ነው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30 /ሰላሳ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ከግ/ፋ/ንብ/አስተዳደር ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት አቅርቦት የሚሞሉትን ማንኛውንም ግብር ጨምሮ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በደም ባንኩ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ አንድ በመቶ በማስያዝ ከዋናው ፖስታ ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በቀረበው የመጫረቻ ሰነድ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ መሰረት ብቻ የአንድ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማ እና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደም ባንኩ የግዥ ኦፊሰር ቢሮ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደም ባንኩ ቢሮ ይከፈታል፣ ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ቢሮ በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 15 37 /058 220 74 03 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. አድራሻ ቀበሌ 08 ከሰላም ካምፓስ ፊት ለፊት የድሮው አውስኮድ ግቢ ውስጥ ይገኛል፡፡

የባህር ዳር ደም ባንክ አገልግሎት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here