ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
106

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት ሎት 1 የቢሮ እድሳት የፊኒሽንግ ዕቃዎች እና ሎት 2 የፊኒሽንግ ሥራ የእጅ ዋጋ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ አግባብ ያለው እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከ200.000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የግዥው ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የአብክመ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን ቢሮ ቁጥር 223 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአብክመ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን (ANRS Transport & Logistics Authority) በሚል ስም ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ሎት 1 የቢሮ እድሳት የፊኒሽንግ ዕቃዎች እና ሎት 2 የፊኒሽንግ ሥራ የእጅ ዋጋ በጥንቃቄ በመለየት በታሸገ ፖስታ በአብክመ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በአብክመ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን ቢሮ ቁጥር 001 የካቲት 25 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ይታሸግና በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30  ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊ ድርጅት የሚመረጠው በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ድርጅት ይሆናል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን ቁጥር 001 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 64 27 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን

ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here