የመርሳ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ልጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት የሚሰሩ መሰረተ ልማት ሥራዎች መካከል ሎት 1 02 እና 03 ቀበሌ ከሞላ ይመር ቤት እስከ ከድጃ ጀማል ቤት ድረስ 850 ሜትር አዲስ ጠጠር መንገድ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በዘርፋ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ፡፡
- የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሥራ ልምድ ማስረጃ በመንግስት የሥራ ቋንቋ በአማርኛ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ደረጃ 5(አምስት) እና በላይ የሙያ ፈቃድ ያለው (ደረጃ 6፣7፣8፣9 አያካትትም)፡፡
- የሚጫረቱበት ጨረታ ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ /የቫት/ ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ያላቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 120,000 /አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ወይም በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬድት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አያይዘዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-8 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ዋጋ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የሥራዉን ዝርዝር መግለጫ ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ያችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሀሳብን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመርሳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ወይም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት 10/06/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 09/07/2017 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በ31ኛው ቀን በ10/07/2017 ቀን በ3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አይስተጓጎልም፡፡ የጨረታ መክፈቻው የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ሥራ ቀን በተቀመጠው ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ወይም 09 14 46 10 24 /09 35 21 25 15 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የአሸነፋቱን ሎት የማቴሪያልና የጉልበት ወጪ በተጫራቾች የሚሸፈን ነዉ፡፡
- ሥርዝ፣ ድልዝ እና ፍሉድ መጠቀም አይቻልም፡፡ ከጨረታ ዉጭ ያደርጋል፡፡
- የጨረታ ዋጋ ጸንቶ መቆያ ጊዜ ጨረታዉ ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ለ60 ቀን የጸና ይሆናል፡፡
- 3 እና ከዚያ በላይ ተወዳዳሪዎች ከቀረቡ አርቴሚቴክ ዉጤት ልዩነት ከሁለት ነጥብ አምስት በመቶ በላይ ከመጣ ተቀባይነት የለዉም ከ3 በታች ተወዳዳሪዎች ከቀረቡ ከአንድ በመቶ በላይ የአርቲሜቲክ ልዩነት ተቀባይነት የለዉም፡፡
የመርሳ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት