ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
93

እብናት ወረዳ ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት ለእብናት ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል በህበረት 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ግቢ ውስጥ G+1 ባለ 10 የመማሪያ ክፍል ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  4. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ዋጋ ድምር ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በእብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ጋራንት (በጥሬ ገንዘብ እብናት ወረዳ ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት ዋና  ገ/ያዥ ገቢ በማድረግ ግቢ የሆነበትን የገቢ ደረሰኝ ከኦርጅናሉ የጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
  7. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አድርጎ ኦርጅናል ሰነድ እብናት ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግዥና/ን/አስ/ቡደን መሪ ቢሮ ቁጥር 06 ባዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታዉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ ለ21 ቀን ዉሎ በ22ኛው ቀን ይከፈታል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች (ህጋወዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም በግዥና/ን/አስ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 06 ጨረታው በወጣ በ22ኛው ቀን 8፡30 ታሻጎ 9፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ (የህዝብ በዓል ከሆነ) በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፈዉ ለሥራ በተፈለገበት ስዓት ለ3 ቀናት ተጠብቆ ካልቀረበ በመመሪያ መሰረት መ/ቤቱ እርምጃ የመዉሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝር ከሚሞሉበት ሰዓት ሥርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የጠፋ ከሆነ ከጨረታ ዉጭ ይደረጋል፡፡
  11. የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 08 የማይመለስ ብር 500 /አምስት በመቶ ብር/  በመክፈል ሰነዱን መግዛት  ይችላሉ፡፡
  12. ደረቅ ቸክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
  13. አሽናፊዉ አሽናፊነቱን እንደተገለፀለት ክ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መዉሰድ አለበት፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን  መሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለዉ፡፡
  15. ጨረታዉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 30 ቀን ይሆናል፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 440 06 06 /218 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእብናት ወረዳ ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here