ከአንድ ሺህ በላይ ፕሮጀክቶች እንደሚጠናቀቁ ተገለጸ

0
111

የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ከሰሞኑ ተካሂዷል:: የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የክልሉን መንግሥት የስድስት ወራት የልማት እና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት በክልሉ በበጀት ዓለመቱ አንድ ሺህ 40 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች ይጠናቀቃሉ:: ለነዚህ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያም 17 ነጥብ 43 ቢሊዮን ብር መመደቡን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው አስታውቀዋል::

ክልሉ ከተመደበለት 150 ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ ባሳለፍናቸው ስድስት ወራት 34 ነጥብ  አራት ቢሊዮን ብር ወጭ ተደርጓል።  ከዚህ ውስጥ ለመደበኛ ሥራዎች ማስፈጸሚያ 30 ነጥብ 79 ቢሊዮን ብር ወጭ ተደርጓል። ቀሪው ሦስት ነጥብ 59 ቢሊዮን ብር ደግሞ ለካፒታል ሥራዎች (ለፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ) መውጣቱን ተናግረዋል::

ርእሰ መስተዳድሩ እንዳሉት ያለውን ውስን ሃብት በመጠቀም የተጀመሩ የካፒታል ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ በዚህ ዓመት ለመመረቅ እና ወደ ልማት ለማስገባት ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል። ።

(ሳባ ሙሉጌታ)

በኲር የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here