ኮርፖሬቱ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

0
111

ንጋት ኮርፖሬት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል፤ ኮርፖሬቱ ይህንን ትርፍ ማግኘቱን ያሳወቀው የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው፡፡ በጉባኤው ላይ የንጋት ኮርፖሬት የሥራ አፈጻጸምን የኮርፖሬቱ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ (ዶ/ር) አምላኩ አስረስ ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት አንድ ቢሊዮን 792 ሚሊዮን 18 ሺህ ብር የተጣራ ትርፍ ተገኝቷል፡፡ እንደ ሪፖርቱ ከሆነ   ተቋሙ በበርካታ ዓለም አቀፍ እና ሀገራዊ ፈተናዎች ውስጥም ቢሆንም ውጤታማ ቢዝነስ እና ኢንቨስትመንቶችን  እያካሄደ ነው።

ንጋት ኮርፖሬት  የምርት ሺያጭ ገቢው 10 ቢሊዮን 250 ሚሊዮን 949 ሺህ ብር የደረሰ ሲሆን ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የአንድ ነጥብ 87 ቢሊዮን ብር እድገት እንዳሳየ ነው የተገለጸው፡፡ ሙሉ በሙሉ ባለቤት ከሆነባቸው ኩባንያዎች ብቻም 540 ሚሊዮን 934 ሺህ ብር የትርፍ ግብር በታማኝነት መክፈሉ ተመላክቷል፡፡

በሪፖርቱ እንደተመላተው ኮርፖሬቱ የክልሉን የገበያ ጉድለቶች ለመሙላት በአጠቃላይ አንድ ነጥብ 25 ቢሊዮን ብር የዋጋ ግምት ያላቸው ሸቀጦችን በማቅረብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ ሠርቷል። በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁለት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በየክልሎች አጓጉዟል፡፡ በዚህም “የግብርና ልማት አጋር” ተብሎ የወርቅ ዋንጫ መሸለሙን በሪፖር ተመላክቷል፡፡

(ሳባ ሙሉጌታ)

በኲር የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here