ሻላ ሐይቅ

0
134

የሻላ ሐይቅ በጥልቀት እንዲሁም በውኃ መጠን ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ሐይቆች መካከል የመጀመሪያውን ቦታ ይይዛል።

ሐይቁ በዋናው የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ይካለላል። ከባህር ወለል በላይ አንድ ሺህ 559 ሜትር ከፍታም አለው። ከአዲስ አበባ በስተደቡብ፣ በሞያሌ መንገድ 225 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

የሐይቁ ርዝመት 27 ኪሎሜትር፣ አጠቃላይ ስፋቱ ደግሞ 314 ኪሎ ሜትር ስኩዌር ነው። የሻላ ሐይቅ ጥልቀት226 ሜትር ሲሆን በተደጋጋሚ አማካይ ጥልቀት ደግሞ 86 ሜትር ነው።

ሐይቁ የሚይዘው የውኃ መጠን 38 ቢሊዮን ሜትር ኩብ እንደሆነም ይገመታል። ይህ የውኃ መጠን በሌሎቹ የኢትዮጵያ ሐይቆች ማለትም ጣና፣ ዝዋይ፣ አብያታ፣ ላንጋኖ እና የአዋሳ ሐይቆች በአንድ ላይ ሆነው ከሚይዙት የውኃ መጠን እጅግ የላቀ ነው።

ምንጭ፦ www.wikimapia.org

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

 

 

 

 

 

 

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here