ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
101

የጨረታ ቁጥር አብክመ/ግምመገማ/ግጨ/01/2017

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና  ምርቶች መዳረሻ ገበያ ማዕከል  ለአገልግሎት የሚውሉ ማለትም፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች እና መኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሎት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማዕከሉ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 35 ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ምድቦች /ሎቶች/ አንድ በመቶ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም የሚያስይዙት ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ የግብርና  ምርቶች መዳረሻ ገበያ ማእከል  የተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በመግዛትና በመሙላት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ የግብርና ምርቶች መዳረሻ ገበያ ማዕከል በግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 35  ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በዓል ወይም የሥራ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  10. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ኖክ አካባቢ ከፍታ ውሃ ማከፋፈያ ከሚገኝበት ዳቢት ሪል ስቴት ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 35 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 76 69 07 /09 18 48 84 88 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአብክመ ግብርናና የአግሮፕሮሰሲንግ  ምርቶች መዳረሻ ገበያ ማዕከል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here