ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
96

የጨረታ ቁጥር አብክመ/ወኩምኤ/ብግጨ//03/2017

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት ለአገልግሎት የሚውሉ ታብሌት እና ጃምቦ ኬንት ተቀማጩ PZ-3 ተሸከርካሪ ወንበር ሜሽ ሃይባክ ባለ መረብ ጀርባዉ ብረት መወጠሪያ ያለዉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በተናጥል ለመግዛት በተጨማሪም የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች እና የፈርኒቸር እቃዎች መግዛት ይፈልጋል ስለሆነም አገልግሎቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ምድቦች /ሎቶች/ አንድ በመቶ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም የሚያስይዙት ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት የተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ከተጠቀሱት ዕቃዎች ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከአንድ ቴክኒካል እና ከአንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል በተጨማሪ አንድ ቅጅ ቴክኒካል እና አንድ ቅጅ ፋይናንሻል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት በግዥና ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይም ቢሮ ቁጥር 406 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት በግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 406 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በዓል ወይም የሥራ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. አገልግሎት መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 406 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 31 58 ፋክስ 058 320 11 83 ፖ.ሳ.ቁ 965 በመደወልና በመላክ ማግኘት ይቻላል፡፡

የአብክመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here