የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
80

ሁለተኛ ዙር

በደቡብ ወሎ ዞን የወገልጤና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረት ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ በሊዝ በሚደነግገው አዋጅ  ቁጥር 721/2004

አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 እና 2 ደንብ ቁጥር 103/2004 መመሪያ ቁጥር 1/2005 መሰረት በ2017 በጀት አመት 2ኛ ዙር ጨረታ ለሁለገብ ሆቴል

አገልግሎት ለሁለገብ ሆቴል አገልግሎት B+G+7 እና በላይ ግንባታ የሚውል 1 (አንድ) ቦታ ለ3ኛ ጊዜ፣ 2. ለሆቴል አገልግሎት G+4 እና በላይ ግንባታ

የሚውል 1 (አንድ) ቦታ ለ2ኛ ጊዜ፣ 3. ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል G+0 እና በላይ ግንባታ የሚውል 2 ሁለት ቦታዎች 2ኛ ጊዜ፣ 4 ለመኖሪያ

አገልግሎት የሚውል G+0 እና በላይ ግንባታ የሚውል 3 (ሶስት ቦታዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ማንኛውም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

  1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሽህ ብር/ በመክፈል ወገልጤና ከተማ አሰተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይቻላል፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ብቻ ወገልጤና ከተማ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው ሳጥን ይሆናል፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው የሥራ ቀን 11፡00 ላይ ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወገልጤና ከተማ አስተዳደር አዳራሽ ውስጥ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች ሰነድ በሚገዙበት ጊዜ ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው መጠን፣ የጠቅላላ የቦታው ስፋት በመነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኝው ውጤት ከሰላሳ በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖረባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚቀርቡትን የጨረታ ሰነዶች በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መሰረት ማሰቀመጥ አለባችው፡፡ ተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መሰረት ያልቀረበ ጨረታ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይሆናል፡፡ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የገዙዋቸውን የጨረታ ሰነዶች ሁሉንም ኦርጅናል መረጃ በሠም በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከፖስታ ውጭ የሚቀርብ መረጃ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. የጨረታ አሸናፊውን ለመለየት የማወዳደሪያ መስፈርቶች መሰረት በማድረግ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ለቦታው ያቀረቡት ዋጋ ሰማኒያ በመቶ የሊዝ ቅድመ ክፍያ መጠን ጋር ሃያ በመቶ የሚያዝ ይሆናል፡፡
  10. የግንባታ መጀመሪያና ማጠናቀቂያ ጊዜ በመመሪያ ቁጥር 1/2005 አንቀፅ 47/49 የተቀመጠ ቢሆንም ግንባታውን ገንብቶ በአጭር ጊዜ የሚያስረክብ መሆን አለበት፡፡
  11. ቦታውን ማየት ለሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገልፅ መረሀ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
  12. መ/ቤቱ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ያወጡትን ወጭ የመጠየቅ መብት አይኖራቸውም፡፡
  13. ጨረታውን በበኩር ጋዜጣ ዌብ ሳይት ፣ ቴሌግራም እና የፌስቡክ ገጽ ላይ ማየት ይችላሉ፡፡
  14. በጨረታው ሰነድ አሞላልና የጨረታ ስነ ስርዓት ላይ ማብራሪያ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ባለው የሥራ ቀን ለተጫራቾች ገለጽ ይደረጋል፡፡
  15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 335 05 20 በሞባይል ቁጥር 09 20 44 19 35 ወይም 09 20 48 42 62 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የወገልጤና ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here