በአፈ/ከሳሽ እነ ሂሩይ ሲሳይ እና በአፈ/ተከሳሽ ጌቴ ይጀቡ መካከል ስላለው የአፈፃፅም ክስ ክርክር ጉዳይ በአዲስ አለም ቀበሌ ጌቴ ይጀቡ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው በካርታ ቁጥር 7449/2014 በአዋሳኝ በምሥራቅ – ፣ በምዕራብ – ፣ በሰሜን – እንዲሁም በደቡብ – ስፋቱ 250 ካ.ሜ ግምቱ 2,449,334.6 /ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ አርባ ዘጠኝ ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ አራት ብር ከስድስት ሳንቲም/ ይሸጣል፡፡ ስለሆነም በ20/07/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ በግልጽ ጨረታ ስለሚሸጥ መጫረት የምትፈልጉ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በሰዓቱና በቦታው በመገኘት ተመዝግባችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የመጨረሻ አሸናፊው ያሸነፈበትን ¼ ኛውን ወዲያውኑ በሞ/85 ማስያዝ የሚጠበቅበት መሆኑን ፍ/ቤቱ ያሳውቃል
የባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት