የላይ ጋይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን በ2017 ዓ.ም በጀት አመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ምድብ 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ምድብ 2 በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በላይ ጋይንት ወረዳ ከቀበሌ 13 ከአንጠባጥቤ እስከ ደምበጣ ገብርኤል ድረስ ለሚሰራው መንገድ ከደረጃ 5 በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መወዳደር የሚፈልጉ ማንኛውም ድርጅት መጫረት የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፡-
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ /ቲን/ ነበር ያላቸው፡፡
- የሚያቀርቡት እቃ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነትን የማረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለመንገድ ሥራው የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳታፍ ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙት እቃዎች አይነትና የሚሰራው መንገድ ሥራ ዝርዝር መግለጫ /ሰፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ላይ ጋይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ እና ንብረት አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን እና የመንገዱን ሥራ ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ እና በጥሬ ገንዘብ በመሂ1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለእቃዎቹ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ኦርጅናልና ቅጅ በማለት በተለያዩ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ላ/ጋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ3፡30 ይዘጋና በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላ/ጋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በ16ኛው ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- ለመንገድ ሥራው ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ኦርጅናልና ቅጅ በማለት በተለያዩ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ላ/ጋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ22ኛው ቀን በ3፡30 ይዘጋና በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላ/ጋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በ22ኛው ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ አይስተጓጐልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈውን እቃዎች በየፑሉ ማድረስ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ዋጋ ነው፡፡
- በማስታወቂያ ያልተገለፁ ሌሎች ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- ከሎቱ ውስጥ ያንዱን ዋጋ ካልሞሉ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- ሥለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ላ/ጋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 445 13 99 /058 445 00 05 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
የላይ ጋይንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት