ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
90

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር በ2017 ዓ.ም በመደበኛ ማስፈፀሚያ በጀት ለሴክተር መሥሪያ ቤቶች ምድብ 1 የጽህፈት መሳሪያ እቃ ግዥ ፣ ምድብ 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃ ግዥ እና ምድብ 3 የጭነት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በነፃ ኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የገንዘብ መጠን አንድ በመቶ እና ከዚያ በላይ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በጥሬ ገንዘብ በግዥ እና ንብረት አስተዳደር ስም በመክፈል የተከፈለበትን ደረሰኝ ከሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ አሽገው ኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ላይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ 16 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱ ክፍት ሆኖ ይቆያል ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ላይ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  9. የእቃ ርክክብ ቦታ የሚደረገው ኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት እስቶር ድረስ ይሆናል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ለውል ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን አስር በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. የተወዳዳሪዎች መመሪያ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ ይገኛል፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 እና ቢሮ ቁጥር 14 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 00 41 59 24 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
  13. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here