ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
93

የግዥ መለያ ቁጥር  አብክመ/ሳቴኮ/ግ/ጨ/04/2017

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ለተለያዬ  አገልግሎት የሚውሉ ሶፍትዌሮችን ማለትም፡- ሎት 1  የፕሮጀክት አስተዳደር ሲስተም ሶፍትዌር ልማት፣ ሎት 2 የሰው ሃብት አስተዳደር ሲስተም ሶፍትዌር ልማት፣ ሎት 3 የመንግስት ሰራተኞች የመረጃ አስተዳደር ሲስተም ሶፍትዌር ልማት፣ ሎት 4 የፍትህ ጉዳች አስተዳደር ሲስተም ሶፍትዌር ልማት እና ሎት 5 የቱሪዝም አስተዳደር ሲስተም ሶፍትዌር ልማት በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስለማት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ህጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉለት ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የሚወዳደሩበት ሎት ግዥ ጥቅል ዋጋ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከቴክኒካል ስፔሲፊኬሽን ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚለሙ ሶፍትዌሮችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ቴክኒካል ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች በተቋሙ ዋ/ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣትና የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ወይም መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበትን የሲስተም ልማት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነዳቸውን፣ የንግድ ፈቃድ ሰነድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና ተያያዥ ሰነዶችን በጥንቃቄ በታሸገ  ፖስታ እንዲሁም የፋይናንሻል (የዋጋ) ሰነዳቸውንና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በሌላ ፖስታ በማድረግ ለየብቻ በታሸጉ 2 ፖስታዎች (ቴክኒካልና ፋይናንሻል በማለት)  ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከቀን 17/06/2017 ዓ.ም እስከ 01/07/2017 ዓ.ም ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በ01/07/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 20 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው የሚለየው በሎት (ምድብ) ዋጋ  ይሆናል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነዳቸውና የፋይናንሻል ሰነዳቸው ላይ የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ካላደረጉ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 68 56 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን

ባህርዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here