ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የአነደድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ከSLM-KFW ፕሮጀክት ከተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ፖሊተን ቲዩብ በግልጽ ጨረታ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ነጋዴዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን ከ200000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከአነ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በገንዘብ ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን /ቢድ ቦንድ/ በአንድ ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አሽገው የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም  አድራሻና ፊርማ በመሙላት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ በአነደድ ወረዳ ግ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት የሚችል ሲሆን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 የሚከፈት ይሆናል፡፡ 16ኛው ቀን  የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሰሳይ ሰዓትና ቦታ ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የሚከፈት ሲሆን የጨረታ ሳጥኑን በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ የጨረታ ሳጥኑን ሲከፈት ሳይገኙ ቢቀሩ ጨረታውን ከመክፈት የሚያስተጓጉል አይሆንም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ያልተገኙ ተጫራቾች  በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚይዝበት ወቅት የአሸነፈበትን እቃ /ንብረት/ ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች የአሸነፉትን እቃ /ንብረት/ ጠቅላላ ወጭውን በመሸፈን አነደድ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ የሚችል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች ጨረታ አሸንፎ ሲመጣ ዉል ለመያዝ የሚያስፈልጉ ወጭዎችን መሸፈን ይኖርበታል፡፡
  11. ዉድድሩ በጥቅል ዋጋ /በሎት/ ይሆናል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አነደድ ወረዳ ግ/ል/ጽ/ቤት የግብርና ግብ/ገጠ/ፋይ/አገ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 261 00 00 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

የአነደድ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here