ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
82

በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ. የስኳር ማጓጓዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ለአንድ ዓመት ዉል ይዞ የሚያጓጉዝ ሁኖ በየዙሩ (በየወሩ) 978 ኩ/ል 1ኛ. ከመትሃራ ስኳር ፋብሪካ ወደ ባ/ዳር ከተማ፣ 2ኛ. ከአዲስ አበባ ወደ ባ/ዳር ከተማ ዉል በመያዝ ማጓጓዝ የሚችል ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ /ዋስትና/ ወይም /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ግልጽ ጨረታው ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ በማስገባት ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
  6. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 350 /ሶስት መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  8. ቅዳሜ ዩኒየኑ የሥራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ጨረታው ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. አሽናፊ የሚለየው በተናጥል ሲሆን የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመረመረ (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል /ይሸፍናል፡፡ የሚጓጓዘውን አይነት መጠንና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ይሆናል፡፡
  12. የትራንስፖርት ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሸከርካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ከ70 ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሁነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡
  13. የስኳር የትራንስፖርት ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች የተሸከርካሪ ዝርዝር፣ የስሌዳ ቁጥር የመኪናው አይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ ወቅታዊ የታደሰ ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  14. በስኳር ማጓጓዝ የትራንስፖርት ጨረታ ተሳታፊ በመንገድ ላይ የሚከሰተውን ማንኛውም ወጭ አሸናፊው ይሸፍናል፡፡ የሚጓጓዘውን የስኳር መጠንና የርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
  15. የስኳር ማጓጓዝ ጊዜው እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ/ም ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  16. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  17. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 11 59 05 34 /09 18 27 83 96 መጠየቅ ይቻላል፡፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here