የጨረታ ማስታወቂያ

0
98

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት  ፍትህ  ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት  የብስክሌት ጐማ ከነካላማዳሪው ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)  ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ሲያቀርቡ የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ የሌለው ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. የተለያዩ የብስክሌት ጐማ ከነካላማዳሪው ለማቅረብ የሚሳተፋ አቅራቢዎች የጨረታ ሰነዱ በተለያየ ፖስታ ታሽጐ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል አብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የብስክሌት ጐማ ከነካላማዳሪው ብር 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማለት ከ17/06/2017 እስከ 01/07/2017 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 04 በ16ኛው ቀን 02/07/2017 ዓ.ም 3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ፍትህ  ቢሮ

ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here