በአማራ ክልል በ2016/17 የምርት ዘመን አምስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ ከ169 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ማግኘት መቻሉን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል::
ከሮው የማሕበራዊ ትስስር ገጽ ባገኘነው መረጃ ቢሮው የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ከዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊዎች እና ቡድን መሪዎች ጋር በባሕር ዳር ከተማ ገምግሟል:: የቢሮው ምክትል ኃላፊ አጀበ ስንሻው እንደገለጹት ይህ ምርት ሊገኝ የቻለው የዝናብ አጀማመሩ እና ስርጭቱ ለሰብል ልማት ተስማሚ ስለነበር ነው:: እንዲሁም ምርትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ግብዓቶችን እና ቴክኖሎጅዎችን አርሶ አደሩ በአግባቡ ስለተጠቀመ ጭምር ነው:: ሰባት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያም ለአርሶ አደሮች ተከፋፍሎ እንደነበር ጠቁመዋል:: ክልሉ የበቆሎ፣ ጤፍ እና ስንዴ ምርጥ ዘር አቅርቦት ላይም የራሱን ፍጆታ ከመሸፈን ባለፈ ለሌሎች ክልሎች ጭምር መትረፉ ተገልጧል::
በምርት ዘመኑ 169 ሚሊዮን ኩንታል ለማግኜት መታቀዱ ይታወሳል፤ ከዕቅዱ በላይ ምርት መገኘቱንም የቢሮው መረጃ አመላክቷ ል::
(ሳባ ሙሉጌታ)
በኲር የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም