በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረ ታቦር ከተማ የፋርጣ ወረዳ ፍ/ቤት የሚገለገልባቸው ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 4 የህትመት ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 20 /ሀያ ብር/ በመክፈል በመ/ቤታችን ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ከዋና ገ/ያዥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃ ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ኦርጅናል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ፋ/ን/አ/ስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 2፡59 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 3፡00 ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይታሸጋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በ16ኛዉ ቀን 3፡30 ጨረታው ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዚጊያና መክፈቻ በበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራች በጨረታዉ አሸናፊ ከሆናችሁ በኋላ የምታቀርቡት ደረሰኝ የድርጅቱ ስም፣ ስማችሁ እና የንግድ ፈቃድ አይነት በህትመት የተዘጋጀዉ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ በጨረታ ከሚገዛዉ እቃ መጠን ሃያ በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች እቃዉን በሎት /በጥቅል/ የሚፈፀም መሆኑ ታዉቆ በእያንዳንዱ ዝርዝር እቃዎች መሙላት ይኖርበታል፡፡ የተዘረዘሩት እቃዎች በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታዉ ዉጭ ይደረጋል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የሞላዉን ጠቅላላ ዋጋ ቫቱን ጨምሮ አስር በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በማስያዝ ዉል መፈፀም ይኖርበታል፡፡
- የንብረት ርክክቡ የሚፈፀመዉ ፋርጣ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የማጓጓዣ ወጭን እና የጉልበት ወጭን በተመለከተ አሸናፊ ድርጅቱ ይሸፍናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 24 46/ ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የፋርጣ ወረዳ ፍርድ ቤት