ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
83

በአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለ2017 በጀት አመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚዉሉ የኢንቨርተር ዕቃዎች አቅርቦት እና የአጥር በር እድሳትና ጥገና ሥራ ከረጂ ድርጅቶች በተገኘ የበጀት ድጋፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መሰፈረቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ለእድሳትና ጥገና ሥራ ደረጃ 8 እና በላይ የታደሰ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ካርድ/ ወይም ተከታታይ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. የግዥው መጠን ብር 200,000, /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታውን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ መሰረት የአንዱን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ድምር ዋጋ ከነ ቫቱ በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ኢንስቲትዩቱ ባዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱ የሚሸጠዉ ጨረታዉ ከወጣበት ቀን እስከ 15ኛዉ ቀን ከቀኑ 11፡30 ብቻ ይሆናል፡፡
  10. ጨረታዉ በ16 ኛዉ ቀን የጨረታ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 3፡35 ላይ ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000 በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ፣ በባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  12. ኢንስቲትዩቱ የጨረታ አሸናፊዉ ከተለዬ በኋላ እንደ ተቋሙ በጀት ሃያ በመቶ በመጨመር ወይም በመቀነስ ውል ይዞ የማስቀረብ መብት ይኖረዋል፡፡
  13. የጨረታው አሸናፊዎች የሚለየው በሎት ምድብ በድምር ዋጋ ይሆናል፡፡
  14. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 32 38 በሥራ ሠዓት በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
  16. ኢንስቲትዩቱ የሚሰበስበው ሁለት በመቶ ዊዝ ሆልድ ብቻ ነዉ፡፡

አድራሻ፡- ፈለገ ህይወት ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ጎን

የአብክመ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here