የጨረታ ቁጥር፡- አብክመማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን/ግጨ/03/2017 ዓ.ም
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የ2017 በጀት አመት ለኮሚሽንና በሥሩ የሚገኙ ለዞኖችና ወረዳዎች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ ለ4 ወር (ለተከታታይ 120 ቀናት) በሚቆይ ግዥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- ሬንጀር ኮትና ሱሪ ከነመለዮው፣ ሬንጀር ሸሚዝና ሱሪ ከነመለዮው፣ የሬንጀር ቲሸርት፣ ሬንጀር ጃኬት፣ የዝናብ ልብስ ቢሮ ተመድበው ለሚሰሩ ከሬንጀር ደንብ ልብስ ጋር የሚመሳሰል፣ የዝናብ ልብስ በጥበቃ ተመድበው ለሚሰሩ ከሬንጀር ደንብ ልብስ ጋር የሚመሳሰል ባለ 3 /ሶስት/ ቀዳዳ፣
- መደበኛ የደንብ ልብስ ሸሚዝና ሱሪ፣ መደበኛ የደንብ ልብስ ቡላማ ቲሸርት፣ የስትራቴጂክ መኮንኖች ፊልድኬፕ፣ የብሉብላክ መደበኛ ልብስ ከፍተኛ መኮንኖች ፊልድ ኬፕ፣ የብሉ ብላክ መደበኛ ልብስ የመካከለኛ መኮንኖች ፊልድ ኬፕ፣ የብሉ ብላክ መደበኛ ልብስ የዝቅተኛ ማዕረግተኞች ፊልድኬፕ፣ ብሉ ብላክ ፊልድ ጃኬት፣
- ቬሪ ቮኔት መለዮ፣
- ከቆዳ የተሰራ የወንድና የሴት ቦት ጫማ ከነ ዚፑ፣ ከቆዳ የተሰራ የወንድ ጉርድ ጫማ፣ከቆዳ የተሰራ የሴት ጉርድ ጫማ፣
- የእግር ካልሲ ረዥሙ እና የእግር ካልሲ አጭሩ፣
- ጥቁር የሸራ ወታደራዊ ቀበቶ እና ስሊፒንግ ባግ፣
- የመኮንኖች ኮርደን፣ የሱፍ ካፖርት፣ ፍሎቨር ሹራብ፣ በትክሻ ላይ የሚንጠለጠል ፊሺካ እና ጥቁር ሰማያዊ ቀጭን ኮርደን፣
- የእጀባ ፖሊስ አባላት ተለባሽ የትጥቅ መያዣ እና በቀበቶ ላይ የሚንጠለጠል ቦርሳ፣
- ግራንድ ዩኒፎርም የተሟላ፣
- ብርድ ልብስ የውጩ፣ ለሙያ ስልጠና የሚሆን የተለያዪ ጨርቆች እና የተለያዪ አይነት የመኪና ጎማዎች፣
በዚህም መሰረት ኮሚሽኑ የሚከተሉት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- አምራቾች የአምራችነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ወይም ድርጅቶች አቅራቢ ከሆኑ ከአምራቹ የተሰጠ የ2016 ዓ.ም ዉክልና እና ምርቱ በትክክል የአምራቹ መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ እንዲሁም አሸናፊ ከሆነ በኋላ ውል መያዝ የሚችለው በተወዳደረበት የአምራችነት ውክልና መሰረት መሆኑ ታውቆ ምርቱን ወደ አብክመ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ማስገባት የሚችለው ሲወዳደር ውክልና ከሰጠው ድርጅት ማስረጃ ሲያቀርብ ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቾች የደንብ ልብሱን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 17 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሌሎች እቃዎች ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 00 (አንድመቶብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 17 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ አይተም (አይነት) ማስያዝ የሚገባቸው ሲሆን፤ በባንክ በተረጋጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ህጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን