ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

የዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተለያዩ የእድሳት ስራ ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ እና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
  4. ማንኛውንም የሚጠየቁትን መረጃ ማሟላት የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው 200‚000 /ሁለት መቶ ሽህ/ብርና ከዚያ በላይ ከሆኑ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ በመምጣት ለእያንዳንዱ 100.00 / አንድ መቶ / ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. በ16 ኛው ቀን ኦርጅናሉን በማስገባት ከጧቱ 4፡30 ላይ የጨረታ ሰነዱ ታሽጎ በዚሁ እለት 5፡00 ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች በሚሞሉውት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረብ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን እንዲሁም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትን ሙሉ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት ተቋራጮች ደረጃቸው ከደረጃ ከ7-GC/BC እና በላይ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
  12. የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  13. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ሲገለጽ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10በመቶ የውል ማስከበሪያ ሲፒዩ በማስያዝ ውል መፈጸም ይኖርባቸል፡፡ ስራው ከተጠናቀቀ እና ክፍያ ከተፈጸመ በኋላ ለተጨማሪ 30 ቀን ፀንቶ ይቆያል፡፡
  14. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ተጫራቾች ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 092 047 88 84 ይደውሉ፡፡

 

የዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here