በአፈ/ከሳሽ ተገኘ ብርሃን እና በአፈ/ተከሳሽ ባንቲገኘ ገነትና ቢሆነኝ አያሌው መካከል ባለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር 03 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ በላይነህ ጌትነት በሰሜን፣ መንገድ እንዲሁም በደቡብ ስንቅነሽ ሙሉ የሚያዋስነው በአፈ/ተከሳሽ ባንቲገኘ ገነት ስም የተመዝግበ ቦታ የጨረታ መነሻ ዋጋ 657,086 /ስድስት መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ ሰማንያ ስድስት ብር/ ስለሚሸጥ መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ወጥቶ እስከ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከ3፡00 እስከ 6፡00 ጨረታው የሚካሄድ መሆኑን አውቃችሁ ቦታው ድረስ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ /በሲፒኦ/ አስይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት