በአዊ ብሄረሰብ ዞን የዳንግላ ከተማ መጠጥ ዉሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የገቢ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ለጽ/ቤታችን ለ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. ቧንቧ እና መገጣጠሚያ ዕቃዎች፣ ሎት 2. ኮምፒውተር እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 3. ፓምፕ እና ኤሌክትሮ መካኒካል መለዋዎጫ እቃዎች፣ ሎት 4. የደንብ ልብስ /ብትን ጨርቅ፣ ጫማ፣ ተሰፍተው የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች/፣ ሎት 5. ኖርማል /ሶላር/ መነፀር፣ ሎት 6. የውሃ ጥራት መመርመሪያ ኪት ከአቅራቢ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ ውድድሩ በሎት መሆኑን በማወቅ የጨረታ ሠነዳቸውንና ሌሎች መረጃዎቻቸውን በፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ጀምሮ የሚቆጠር ይሆናል፡፡ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 11፡00 መግዛት እና ማስገባት ይችላሉ ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ እስከ 3:30 ተጫራቾች ጨረታውን በማስገባት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት 4:00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ የድርጅቱን ማህተም፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
- የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ /ማሻሻያ/ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 100 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጽ/ቤታችን ደረሰኝ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ በባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በመቤ/ቱ ደረሰኝ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ከተጠየቀው እቃ ውስጥ ተቋሙ ሃያ አምስት በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ወጭ ዳንግላ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 221 00 56 ወይም 058 221 19 75 ደውሎ ወይም የገቢ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በአካል በመቅረብ መረዳት ይችላሉ፡፡
የዳንግላ ከተማ መጠጥ ዉሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ፅ/ቤት