የጨረታ ቁጥር፡ EEU D/M/R/03/2017
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደ/ማርቆስ ሪጅን ቢሮ እና በሥሩ ላሉ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት የሚያገለግሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ አይነት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
ተ.ቁ | የዕቃዉ ዓይነት | ሎት | የጨረታ ዋስትና
ማስከበሪያ/ሲፒኦ/ |
የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት | የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት | |||
1 | የላፕቶፕ ግዥ ጨረታ | ሎት 1 | 25,000 | መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 | መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30 | |||
2 | የመካኒካል ቱል ኪት ግዥ ጨረታ | ሎት 2 | 12,000 |
|
መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30 | |||
3 | የተለያዩ አይነት የተሸከርካሪ ጎማዎች የግዥ ጨረታ | ሎት 3 | 30,000 |
|
መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30 | |||
4 | የተለያዩ የተሸከርካሪዎች የቅባት አይነት የግዥ ጨረታ | ሎት 4 | 25,000 | መጋቢት 8ቀን 2017 ዓ.ም 8.00 | መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30 | |||
5 | የተለያዩ አይነት የከባድ መኪና ዕቃ መለዋወጫ የግዥ ጨረታ | ሎት 5 | 20,000 | መጋቢት 8ቀን 2017 ዓ.ም 8.00 | መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30 | |||
6 | የተለያዩ አይነት የቀላል መኪና ዕቃ መለዋወጫ የግዥ ጨረታ | ሎት 6 | 20,000 | መጋቢት 8ቀን 2017 ዓ.ም 8.00 | መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30 | |||
7 | የተለያዩ አይነት የፕሪንተር እና የፕሪንተር ቀለም የግዥ ጨረታ /እስቴሽነሪ/ | ሎት 7 | 250,000 | መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም 8.00 | መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30 |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት፤ የአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀትና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ያላቸው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ማርቆስ ሪጅን ቀበሌ 02 እንቦሳ የገበያ ማዕከል ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 13 በመምጣት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በካሽ በመክፈል ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 8/2017 ዓ.ም ድረስ የጨረታው ሰነድ መውስድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የመወዳደርያ ሰነዳቸውንና የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስከበሪያ በሎት በተጠቀሰው መሰረት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ መጋቢት 8/2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 8፡00 ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን መጋቢት 8/2017 ዓ.ም 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም በደብረ ማርቆስ ቀበሌ 02 እንቦሳ የገበያ ማዕከል ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘዉ የሪጅኑ ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር /058 178 46 33/ መደወል ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ማርቆስ ሪጅን