የዕቃ አቅርቦት እና የእጅ ዋጋ ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
162

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ መጠን ያላቸው የቢሮ ሸልፎች ለሥራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ጨምሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ አግባብ ያለው እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከ200.000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚሰሩት የቢሮ ሸልፎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 223 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ (ANRS Plan and Development Bureau) በሚል ስም ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 መጋቢት 09  ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሸጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  11. አሸናፊ ድርጅት የሚመረጠው በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ድርጅት ይሆናል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ ኘላንና ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 001 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 64 27 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here