ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
104

የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በኮሪደር ልማቱ ለፈረሰው ዋናው ገቢ የህንፃ ተቋራጮችን የሙያ እና የጉልበት ዋጋ አውዳድሮ የፈረሰውን አጥር ማስገንባት፣ ለግንባታ የሚሆን የተለያዩ ጥሬ ዕቃዎች የመኪና ዕቃዎችን የተለያዩ ትምህርት ክፍሎች የማሰልጠኛ ዕቃዎችን እና አገልግሎት የሰጡ ቆርቆሮዎችን መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በግልጽ ጨረታ መሳተፍ የሚችሉ፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ሲፒኦ) ያላቸው፡፡
  3. የግዥዉ መጠን ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ የሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስጥር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የህንፃ ተቋራጭ የሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  6. የሚሰራው ሥራ ዝርዝር እና ከላይ የተጠቀሱት የዕቃ ዝርዝሮችን ኮሌጁ ከሚያዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ያገኛሉ፡፡
  7. የጨረታ ዉድድሩ አርትሜሪክ ተሰርቶ አሸናፊው እንዲለይ ይደረጋል፡፡
  8. የጨረታ አሸናፊው ለአሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና /ጋራንት/ በጥሬ ገንዘብ በኮሌጁ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ09/07/2017 ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ09/07/2017 ዓ.ም በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ወይም ገጽ ላይ ፊርማ እና የድርጅቶች ማህተም በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30 እስከ 11፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን ድረስ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመገኘት ወይም ቁጥር 058 111 83 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የለበትም፡፡
  14. የአንድ ቆርቆሮ ዋጋ መነሻ ብር 700 /ሰባት መቶ ብር/ ነው፡፡

የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here