የጨረታ ቁጥር 06/2017
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን /አሚኮ/ ሎት 1 የአይሲቲ ዕቃዎች፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ሎት 3 የጽህፈት መሳሪያ በድጋሜ በግልጽ ጨረታ ዘዴ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፊኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ /የቫት/ ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመግዛት አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 104 መዉሰድ ይቻላል፡፡ ሎት 1 እና ሎት 2 የቴክኒክ እና የፋይናስ ሰነዶችን ለየብቻ በመሙላት ሰነዶችን በሁለት ኮፒ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጅዉ የጨረታ ሣጥን እስከ 16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡ ሎት 3 የፋይናንስ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡ በቴክኒክ ምዘና ለሚያስፈልጋቸው ሰባ በመቶ እና በላይ ያመጡ ድርጅቶች ወደ ፋይናንስ ዉድድር የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚፈለጉት የጽህፈት መሳሪያ፣ የአይሲቲ እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፊኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
ባህር ዳር