ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
87

የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የግብዓት አቅርቦትና ስርጭት ገጠር ፋ/የስራ ቡድን ለመስኖ አት/ፍራ/ዉሀ አጠቃቀም ቡድን አገልግሎት የሚውል የአቡካዶ እና የማንጎ ዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን  በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግብርና መምሪያዉ የግብዓት አቅርቦት እና ስርጭት ገጠ/ፋይ የሥራ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ00  ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ስለዚህ ጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ማለት የዕቃዎቹ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን)፣ በዘርፉ እና በዘመኑ  የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የማቅረቢያ ቦታ፣ የማቅረቢያ ጊዜ፣ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት  ቀን ነዉ፡፡
  9. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን ድረስ መ/ቤቱ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሠዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግብርና መምሪያዉ የግብዓት አቅርቦት እና ስርጭት የሥራ ቡድን ቢሮ 16ኛዉ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል ወይም በፋክስ ቁጥር 058 775 08 81 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 08 71 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የምዕ/ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here