በምሥራቅ ጎጃም ዞን የአነደድ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ለ2017 በጀት አመት ሎት 1 ኮፒውተር እና ተዛማጅ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በ2017 ዓ.ም በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለሚገዙት ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30 /ሰላሳ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት 11፡00 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ የአነ/ወ/ፍ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ተኛው ቀን ድረስ እስከ 2፡59 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 3፡00 ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ 16 በ16ተኛው ቀን 3፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ሆኖም ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባይገኙም ሳጥኑን መክፈት የማንስተጓጎል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታ ሄደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥን መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ወይም /እሁድ እና ቅዳሜ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ መሆን የሚቻለው በሎት በጥቅል ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ተጫራች መሆኑን ታውቆ የሁሉንም እቃዎች ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በዋጋ መሙያው ሰነድ ላይ የድርጅቱ ስም ፊርማ እና ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ ከተዘረዘረው ግዥ መጠን ሃያ በመቶ ሊጨምር /ሊቀንስ ይችላል፡፡
- አሸናፊው ከጠቅላላ ዋጋው ውስጥ አስር በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- አሸናፊው ድረጅት ዕቃውን በራሱ ትራንስፖርት በአነ/ወ/ፍ/ቤት አጎጉዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ /በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቹ በጨረታው ለመወዳደር ላወጣው ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ በስማቸው የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይችሉም፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 63 74 68 17 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአነደድ ወረዳ ፍርድ ቤት