ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
89

በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ዋና ጽ/ቤት ለፎገራ ወረዳ መንገድ ትራንስረፖርት ለሚያሰራው መንገድ ከወርታ ሻጋ ናበጋና ከነጭ አፈር ሽና መድህኒአለም ለሚያሰራው መንገድ ሎት 1 ዶዘር ከነነዳጁ፣ ሎት 2 ኤክስካቫትር ከነነዳጁ እና ሎት 3 ሎደር ከነነዳጁ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በላይ የተገለጹትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ መወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ለምዝገባ በሚመጡበት ወቅት

  1. በዘመኑ የታደሠ በዘርፋ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ካርድ ያላቸው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የጨረታ መጠኑ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴትታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀናት በፎ/ወ/ገ/ኢ/ል/ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ግዥ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 150 /አንድ መቶ አምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና ሙሉ አድራሻ በትክክል በመሙላትና በደንብ ፖስታውን በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከተጠየቁት ማስረጃዎች ጋር በማድረግ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጽ/ቤታችን ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ለሎት 1 ብር 10,000 /አስር ሽህ ብር/፣ ሎት 2 ብር 140,000 /አንድ መቶ አርባ ሽህ ብር/ ሎት 3 ብር 20,000 /ሀያ  ሽህ ብር/ ማስያዝ  ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ጨረታ 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሁኖ ይቆይና 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. 16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና በዚሁ እለት ከጠዋቱ በ4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  6. አሸናፊው አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  7. ሰነዱን ለሚገዙ ተጫራቾች ዝርዝርና ስፔስፊኬሽን ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው ድርጅት ውል እንደያዘ ጨረታ ላላሸነፋት አካላት ተመላሽ ይሆናል፡፡
  9. አንድ ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ ተተንርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  10. አሸናፊው በውሉ መሠረት ከላስረከበ መ/ቤቱ በግዥ መመሪያው መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን መረዳት ይኖርበታል፡፡
  11. በጥቃቅንና አንስተኛ ተደረጅተው ለሚመጡ አካላት ካደራጃቸው ተቋም የድጋፍ ደብዳቤ እና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12. አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
  13. ዶዘሩ ካት D8R ኤክስካቫተሩ የፈረስ ጉልበቱ 350 ሎደሩ XMG/CAT/ ሲሆን ለእያንዳንዳቸው ለ100 ሰዓት እስከ ነዳጁ ነው፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል ከመፈራራሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለፀው መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አሰፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በአሸናፊ ተጫራች የቀረበው በውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ ሃያ በመቶ መቀነስ ወይም መጨመር የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  15. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 446 20 26 በመደወል ጠይቀው መረዳት ይችላሉ፡፡
  16. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የፎገራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ዋና ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here