የጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን ለጉና በጌምድር ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ በመደበኛ በጀት እና በፕሮጀክት በሰቆጣ ቃል ኪዳን በጀት ሎት 1.የግንባታ እቃዎች ፣ ሎት 2. ስሚንቶ ሎት 3.የስፖርት ማቴሪያል እና አልባሳት ፣ ሎት 4. የውሃ እቃ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ በጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17 በመምጣት ለእያንዳንዱ የማይመለስ 50 ብር /አምሳ/ ብር ብቻ በመክፈል ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል ፡፡ ተጫራጮች በጨረታ ሂደቱ ላይ ቢገኙም ባይገኙም ከመክፈት አያግድም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪ ዋስትና የምታስይዙት በቁርጥ የግንባታ እቃው ብር 8,000 /ስምንት ሽህ/ ብቻ ስሚንቶ የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 /አምስት ሽህ ብር/ ብቻ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ 1,500 /አንድ ሽህ አምስት መቶ/ ብር እንዲሁም የውሃ እቃ 8,000/ስምንት ሽህ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ስፒኦ እና በጥሬ ገንዘብ በመሂ -1 በማስቆረጥ በማስያዝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቸች በባንክ ያስያዙትን ማስረጃ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤታችን ገቢ ያደረጉበትን የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ጉ/በ/ወ/ገንዘብ ፅ/ቤት ብለው በመቁረጥ በዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 17 ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ ኦሪጅናል /ዋና/ በታሸገ ፖስታ ጉ/በ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከመ/ቤቱ ቀርቦ ባሸነፈበት ገንዘብ መጠን የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ ያለበት ሲሆን በወቅቱ ቀርቦ ውል ካልወሰደ በግዥ መመሪያው 1/2003 መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡
- የሚገዙትን እቃዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- እቃው የሚቀርበው ወይም ርክክቡ የሚፈፀመው በሙያተኛ ተረጋግጦ ጉና በጌምድር ክምር ድንጋይ ከተማ በእየ ሴክተር መ/ቤቶች ባሉት ንብረት ክፍል ድረስ ነው፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የባዕል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊው የሚለየው በሎት መሰረት በሎት ድምር/ በጥቅል ድምር ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 0582510226 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጉና በጌምድ ገንዘብ ጽ/ቤቱ